Share
Tweet
Pin
Email
Share
Share
Share

የአንድነት ፓርክ ጉብኝት

  • 16/05/2021

በምኒልክ ቤተ መንግስት ቅጥር ግቢ ውስጥ የተሰራውን የ "አንድነት ፓርክ " ለሁሉም ጎብኚ  ክፍት ተደርጓል። ፓርኩ 6 የጎብኝ መዳረሻዎች ያሉት ሲሆን የሃገር በቀል እጽዋትና እንስሳት መገኛ፣ የነገስታቱ እልፍኞች፣ ሙዚየምና ታሪክ ነጋሪ ክፍሎች ተዘጋጅተውለታል።

በዳግማዊ አጼ ምኒልክ እና በባለቤታቸው እቴጌ ጣይቱ በ1878 ዓ. ም. የተመሰረተው ታላቁ የምኒልክ ቤተመንግስት 40 ሄክታር ከሚሰፋው ቅጽር ግቢው ውስጥ 13 ሄክታር ያህሉ ፓርክ ተሰርቶበት ባለፈው ሳምንት በይፋ ተመርቋል። "አንድነት" የሚል ስያሜ የተሰጠው ይሄው ፓርክ ከትላንት ጀምሮ ለማንኛውም ጎብኚ ክፍት ተደርጓል። 

የምኒልክን ቤተ መንግስት እና አንድነት ፓርክን ለመጎብኘት እያንዳንዱ ግለሰብ 6 መቶ ብር፣ አቅም ያለው ደግሞ አንድ ሺህ ብር መክፈል ይጠበቅበታል። የ"አንድነት ፓርክ" ስድስት የጎብኝ መዳረሻዎች ያሉት ሲሆን የሃገር በቀል እጽዋትና እንስሳት መገኛ፣ የነገስታቱ እልፍኞች፣ ሙዚየም እና ታሪክ ነጋሪ ክፍሎች ተዘጋጅተውለታል። "ግቢው ከእነ ግርማ ሞገሱ፤ በታላላቅ እድሜ ጠገብ አጸድ ተክብቦ፤ ምቹ እና አስደሳች ጊዜ ለማሳለፍ ተመራጭ ነው

እነዚህን ሊወዱ ይችላሉ

TripAdvisor

Ratings and Reviews Powered by TripAdvisor