
ወደ ዱባይ የሚጓዙ መንገደኞች
ከሚያዝያ 30 ጀምሮ ወደ ዱባይ የሚጓዙ መንገደኞች ከኮቪድ የነጻ የምርመራ መግለጫ ሰርተፊኬት ኪው አር ኮድ (QR code) ወይም ኤሌክትሮኒክ መግለጫ ፊት ለፊት በሚታይ መልኩ የሌለው ከሆነ ተቀባይነት እንደማይኖረውና ለጉዞ ብቁ እንደማያደርግ ዩናይትድ አረብ ኤምሬትስ ጤና ጥበቃ ሚኒስተር አስታውቋል። ኪው አር ማረጋገጫው የመንገደኛውን ሙሉ ስም እና ውጤት በኮምፒዩተር ኮድ የሚገልፅ ነው፡፡
ስለሆነም የኮቪድ ምርመራ የሚያደርጉበት የህክምና ተቋም የነጻ ሰርቲፊኬት መግጫው ላይ የኪው አር ኮድ (QR code) የተደገፈ ማረጋጫ መስጠት አለበት፡፡
በኢትዮጵያ ውስጥ ይህን አገልግሎት መስጠት የሚችሉ ተቋማት ያሉ ሲሆን እስከአሁን የሚከተሉት የምርመራ ተቋማት ይህንኑ አገልግሎት ይሰጣሉ፣
1. International Clinical Laboratories (ICL)
2. Amin General Hospital
3. Washington Medical Centre
4. ICMC General Hospital